Skip to main content
The Nations, Nationalities, and Peoples' Day

የአዲስ ኮሌጅ ማህበረሰብ አባላት የዘንድሮ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን “ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላም!!” በሚል መሪ ቃል አከበሩ፡፡

የኮሌጁ  ማኔጅመንት  አባላት ፣ መምህራን ፣ ሰራተኞችና  ተማሪዎች  በተገኙበት  ለ17ኛ  ጊዜ  የሚከበረውን  የኢትዮጵያ  ብሔር 
ብሔረሰቦችና  ሕዝቦች  ቀንን  “ሕብረ  ብሔራዊ  አንድነት  ለዘላቂ  ሰላም!!”  በሚል  መሪ  ቃል  ሕዳር 29, 2015 ዓ.ም  በተለያዩ 
ዝግጅቶች  አክብረዉ  ዋሉ፡፡ በዕለቱ  የኮሌጁ  ፕሬዝዳንት  ዶ/ር  መስፍን  ስለሺ  በዓሉን  በማስመልከት  ገለፃ  እና  የእንዃን 
አደረሳቹ  መልእክት  ያስተላለፉ  ሲሆን  በተጋባዥ  ሙሁር  አቶ  ስዩም  ወ/ገብርኤል   የሕብረ-ብሄራዊ  ፌደራል  ስርዓት 
ምንነት፣  ባህርያት  እና  የኢትዮጵያ  ነባራዊ  ሁኔታ  በሚል  ርእስ  በኢ.ፌ.ዴ.ሪ  ፌደሬሽን  ም/ቤት  ለ17ኛዉ  የኢትዮጵያ 
ብሄር፤ብሄረሰቦችና  ህዝቦች  ቀን  
የተዘጋጀ  የስልጠና  ፅሑፍ  ቀርቦ  ከተሳታፊዎች  ጋር  በመወያየት  በቀረበዉ  የስልጠና 
ፅሑፍ  ላይ  ለተነሱ  አስተያየቶች  እና  ጥያቄዎች   ከመድረኩ  መልስ  ተሰጥቷቸዋል፡፡  በተጨማሪም  ተሳታፊዎቹ  ባለፈዉ 
የክረምት  ወቅት  በአረንጓዴ  አሻራ  መርሐ-ግብር  የተተከሉ  ችግኞች  በመጎብኘት  እንክብካቤ  ያደረጉ  ሲሆን  በመጨረሻም 
 
የኢትዮጵያ  ብሔራዊ  መዝሙር  በጋራ  በመዘመር  በዓሉ  ተጠናቛል፡፡

Tags