የአዲስ ኮሌጅ አመታዊ ኤግዚቢሽን
አዲስ ኮሌጅ በ29 ዓመት የማሰልጠን ልምዱ በ2ኛ ዲግሪ በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ማኔጅመንት፣ በፕሮጀክት ማኔጅመንት እና በቢዝነስ አድሜንስትሬሽን፣ በመጀመሪያ ዲግሪ በአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ፣ በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ማኔጅመንት፣ በሲቪል ኢንጅነሪንግ፣ በአርክቴክቸራር አርባን ፕላኒግ እና በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ፣ በቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ከደረጃ 1-4 በአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ፣ በኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፣ በቢዩልዲንግ ኮንስትራክሽን፣ በቢዝነስ እና ፋይናንስ እና አርባንላንድ ማኔጅመንት እያስተማረ ያለ ብቁ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ነው፡፡
በመሆኑም በተቋማችን ውስጥ በቴክኒክና ሙያ ት/ት እና ስልጠና ዘርፍ በ2014 ዓ/ም ለ5ኛ ጊዜ በተዘጋጀ የኤግዚብሽን ፕሮግራም በሁለት የፕሮግራም ይዘት ማለትም በ3 የተመረጡ ርዕሶች ላይ የኮሌጁ ማህበረሰብ የፓናል ውይይት የተካሔደ ሲሆን የውይይቱም አርእስቶች
1ኛ. በቴክኒክና ሙያ ት/ት እና ስልጠና ስትራቴጂን ከመፈፀም አንጻር ኮሌጁ ያለው ሚና ምን ይመስላል፡፡
2ኛ. ከ24ቱ የቴ/ሙ/ት/ስልጠና ስታንዳርድ አንፃር ኮሌጁ ያለበት ሁኔታ እና
3ኛ. የተዘጋጀውን ኢግዚቢሽን በተመለከተ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከውይይቱ ተሳታፊዎች የተነሱ በርካታ ገንቢ የሆኑ አስተያየቶች በመውሰድ የስልጠና ዘርፉን በቀጣይ መሻሻል የሚገባውን ሀሳቦች በመለየት ለሚቀጥለው ዓመት የኢግዚቢሽ ፕሮግራሞች ከዚህ በበለጠ ዝግጅት እንዲሰራ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ ቀጥሎም በሁሉም ዲፓርትመንቶች በተሰሩ የፈጠራ ስራዎች ላይ በሰልጣኞች ሰፋ ያለ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን የኮሌጁ የበላይ ኃላፊዎችም በሰጡት አስተያየት የተዘጋጀው ፕሮግራም ጥሩ እና የሚደነቅ መሆኑን አንስተው በቀጣይ ከዚህ በተሻለ ሁኔታ እና አቀራርብ ሊዘጋጅ እንደሚገባ ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡
በአሰልጣኞች እና ሰልጣኞች የተሰሩ የፈጠራ ስራዎች (ቴክኖሎጂዎች) የኮሌጁ የበላይ ኃላፊዎች በተገኙበት ለኮሌጁ አስተዳደር ሰራተኞች፣ አሰልጣኞች እና ሰልጣኞች ለእይታ ቀርቧል በፕሮግራሙ ተሳታፊ ለሆኑ ት/ት ክፍሎች የእውቅና ሰርትኬት የተሰጠ ሲሆን የተሻለ የፈጠራ ስራዎችን ይዞ ለመጣ እና ለየት ባለአቀራረብ ለፕሮግራሙ ድምቀት ለሆኑ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለመጡ የገንዘብ ማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል፡፡